የሰባቱ ምስጢራተ ቤተ ክርስቲያን

Orthodox Teaching

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሰባቱ ምስጢራት ለምእመናን የእግዚአብሔር ጸጋ የሚሰጥባቸው ቅዱሳን ምስጢራት ናቸው።

በአብ፣ በወልድ፣ በመንፈስ ቅዱስ፣ ሥም በአንድ አምላክ ። አሜን።

መግቢያ

“ሰባቱ ምሥጢራት” የሚለው ቃል በቁጥር ሰባት መሆናቸውን ያመለክታል። እነዚህ ለምእመናን የእግዚአብሔር ጸጋ የሚሰጥባቸው ቅዱሳን ምስጢራት ናቸው። በእነርሱ ተሳትፎ ሰው መንፈሳዊ ሕይወት፣ መፈወስ፣ ቅድስና እና ከእግዚአብሔር ጋር ኅብረትን ያገኛል።

ምሳሌ 9:-1

“ምስጢራት” ተብለው የሚጠሩበት ምክንያቱ የመለኮታዊ ምስጢሮች በመሆናቸው ነው። በውጭ ሲታዩ በቤተ ክርስቲያን የሚፈጸሙ በሥጋዊው አይን የሚታዩ ሥርዓቶች ናቸው፤ በውስጣቸው ግን የማይታየውን የእግዚአብሔር ጸጋ ያሰጣሉ። ሰው ከእኚህ ምሥጢራት ካልተሳተፈ መንግስተ እግዚአብሔርን እንኳን መግባት ሊያይ አይችልም።

ዮሐንስ 3:-3 እና 5

እነዚህም አገልግሎቶች የሚፈጸሙት በእግዚአብሔር እንደራሴ በሆነው በካህኑ ቡራኬ እና ጸሎት አማካኝነት ነው። በጥንታውያን ቤተ ክርስቲያን ሁሉ የታወቁ፣ የታመነባቸው እና የሚሰራባቸውም እነዚህ ናቸው።

ምስጢር 1

ምሥጢረ ጥምቀት

ይህ ከማይደገሙ ምሥጢራት ውስጥ ይመደባል።

  • ጥምቀት ከሥላሴ መወለድ ነው
  • ጥምቀት ወደ ማንኛውም ምሥጢር ለመግባት በር ነው
  • ኃጢአትን የምታስተሰርይ ጥምቀት አንዲት ናት

በጥምቀት ሰው መንፈሳዊ ልደትን ዳግመኛ ይወለዳል እና መንፈሳዊ እድገትን ያስከትላል።

ሕዝ 36:-25 / ሮሜ 6:-3-4 / 1ኛ ቆሮ 6:11

ምስጢር 2

ምስጢረ ሜሮን

ሜሮን ማለት ቅብአት ማለት ሲሆን ከጥምቀት ቀጥሎ ወዲያው የሚፈጸም ምስጢር ነው።

  • አዲስ ቤተ ክርስቲያንና ቅዱሳን ንዋየ ቅድሳት ይቀባሉ
  • ነገስታት በዚህ ይነግሳሉ
  • ከማይደገሙ ምስጢራት ይመደባል

ዘጸአት 30:-22-30 / 1ኛ ሳሙ 10:-1 / 1ኛ ዮሐንስ 2:-20 እና 27

ምስጢር 3

ምሥጢረ ቁርባን

ቁርባን መቅረቢያ፣ መቀራረቢያ፣ መገናኛ ማለት ነው።

  • እርሱ መቀራረቢያ እና መገናኛ ነው
  • ምእመናን በእርሱ ከእግዚአብሔር ጋር ይቀራረባሉ
  • ይህ የምስጢራት ሁሉ መደምደሚያ ነው

በአዲስ ኪዳን ምእመናን የሚያቀርቡት ሥጋ እና ደም በቀር ሌላ መስዋዕት የለም።

ዮሐን 6:-27 እና 53 / 1ኛ ቆሮን 11:-26 / ዕብራ 9:-14

ምስጢር 4

ምስጢረ ክህነት

ክህነት ማለት የአገልግሎት ማዕረግ ሲሆን በጳጳሳት አንብሮተ እድ የሚሰጥ ምስጢር ነው።

  • ከማይደገሙ ምሥጢራት ወገን ነው
  • በአንብሮተ እድ ይተላለፋል

በዚህ ምስጢር ካህናት የማሰርና የመፍታት ሥልጣን፣ ሌሎች ምሥጢራትን የማከብር እና የማቀደስ ሥልጣን ይቀበላሉ።

ማቴዎ 16:-19 / ዮሐን 20:-23 / 1ኛ ጢሞቲ 4:-14

ምስጢር 5

ምሥጢረ ንስሓ

ንስሓ ማለት መጸጸት፣ መመለስ እና ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ማለት ነው።

  • በካህን ፊት ኃጢአትን መናዘዝ
  • የኃጢአት ስርየት መቀበል
  • በሕይወት ሁሉ ሊፈጸም የሚገባ

በዚህ ምስጢር ምእመናን የኃጢአት ይቅርታን ያገኛሉ እና በጸጋ ይታደላሉ።

ምሳሌ 28:-13 / 1ኛ ዮሐን 1:-8-10 / ያዕቆብ 5:-16

ምስጢር 6

ምስጢረ ተክሊል

ምሥጢረ ተክሊል በቤተ ክርስቲያን በካህን ጸሎት እና በረከት የሚፈጸም ቅዱስ ጋብቻ ነው።

  • ተክሊል ወይም ክርስቲያናዊ ጋብቻ
  • በአክሊል የሚወከል ክብር

በዚህ ምስጢር ወንድና ሴት በቅዱስ ጋብቻ ይጣመራሉ እግዚአብሔርም አንድ ያደርጋቸዋል።

ማቴ 19:-3-9 / ኤፌሶ 5:-28-31 / 1ኛ ቆሮንቶ 7:-2-4

ምስጢር 7

ምሥጢረ ቀንዲል

ምሥጢረ ቀንዲል ለታመሙ በጸሎት እና በቅዱስ ቅብአት የሚሰጥ የፈውስ ምስጢር ነው።

  • ለህሙማነ ሥጋ እና ነፍስ የሚሰጥ
  • በካህናት ጸሎት የሚፈጸም

በዚህ ምስጢር እግዚአብሔር ፈውስን እና መመለስን ይሰጣል።

ኢሳ 1:-6 / ሉቃስ 10:-34 / ማር 6:-13 / ያዕቆብ 5:-13-15

ማጠቃለያ

እንግዲህ መንፈሳዊ ህይወት በነዚህ በሰባቱ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን ይመሠረታል በነዚህም ይጸናል። ስለዚህ እያንዳንዱ የሰው ልጅ በነዚህ በርነት እንዲገባ በነዚህ እንዲጸና ሁሉም የማወቅ፣ የማሳወቅ፣ የመፈጸም እና የማስፈጸም መንፈሳዊ ግዴታ አለበት።

2ኛ ጴጥሮስ 1:-10

የእግዚአብሔር ቸርነት የእናታችን የእመቤታችን አማላጅነት ከእኛ ጋር ለዘልዓለም ጸንቶ ይኑር ይቆየን።

The Seven Mysteries

 

Orthodox Teaching

The Seven Mysteries of the Church

In the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church, the Seven Mysteries are holy sacraments through which the grace of God is given to the faithful.

In the name of the Father, and of the Son, and of the Holy Spirit, one God. Amen.

Introduction

The expression “the Seven Mysteries” signifies that they are seven in number. These are the holy mysteries through which the grace of God is bestowed upon the faithful. By participation in them, man receives spiritual life, healing, holiness, and communion with God.

Proverbs 9:1

They are called “mysteries” because they are divine mysteries. Outwardly, they are rites performed in the Church and visible to the bodily eye; inwardly, however, they impart the invisible grace of God. Unless a man partakes of these mysteries, he cannot even see, much less enter, the Kingdom of God.

John 3:3 and 5

These sacred ministrations are performed through the blessing and prayer of the priest, who serves as the steward of God. These are the mysteries known, believed, and practiced in the ancient Church.

Mystery 1

The Mystery of Baptism

Baptism is numbered among the non-repeatable mysteries.

  • Baptism is birth from the Holy Trinity
  • Baptism is the door to all other mysteries
  • There is one baptism for the remission of sins

Through baptism, a man is born again into spiritual life and growth. He receives a spiritual father, heavenly nourishment through the Body and Blood of Christ, and a path toward the Kingdom of Heaven.

Ezekiel 36:25 / Romans 6:3–4 / 1 Corinthians 6:11

Mystery 2

The Mystery of Chrismation

Chrismation follows immediately after baptism. It is not merely an anointing, but a seal that grants the grace of the Holy Spirit.

  • Used to consecrate churches and sacred vessels
  • Used to anoint kings
  • A non-repeatable mystery

Exodus 30:22–30 / 1 Samuel 10:1 / 1 John 2:20, 27

Mystery 3

The Mystery of Holy Communion

Holy Communion is the sacrament through which believers unite with God.

  • It is the act of drawing near and joining with God
  • It is participation in divine life

This is the highest and complete sacrifice — the Body and Blood of Christ — through which believers receive life.

John 6:27, 53 / 1 Corinthians 11:26 / Hebrews 9:14

Mystery 4

The Mystery of Holy Ordination

This mystery refers to priesthood and ministry.

  • A non-repeatable mystery
  • Given through the laying on of hands by bishops

Through ordination, priests receive authority to administer the mysteries, reconcile people with God, and serve the Church.

Matthew 16:19 / John 20:23 / 1 Timothy 4:14

Mystery 5

The Mystery of Penance

Penance is repentance — turning back to God.

  • Confession before a priest
  • Receiving forgiveness of sins
  • Required throughout life

Through this mystery, believers receive forgiveness and restoration through God’s grace.

Proverbs 28:13 / 1 John 1:8–10 / James 5:16

Mystery 6

The Mystery of Holy Matrimony

Holy Matrimony is the sacred union of a man and a woman blessed in the Church.

  • Also called Crowning
  • Symbolized by crowns placed on the couple

Through this mystery, God unites them as one and grants grace for their life together.

Matthew 19:3–9 / Ephesians 5:28–31

Mystery 7

The Mystery of Holy Unction

Holy Unction is the mystery of healing through prayer and anointing.

  • Given to those sick in body or soul
  • Performed by priests through prayer

Through this mystery, God grants healing and restoration.

Isaiah 1:6 / James 5:13–15

Conclusion

The spiritual life is founded upon these Seven Mysteries and strengthened through them. Every believer is called to know them, practice them, and grow through them in faith.

2 Peter 1:10

May the goodness of God and the intercession of Our Lady remain with us forever.